አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደምትደግፍ አስታወቀች

አንቶኒ ብሊንከንመጋቢት 16/2014 (ዋልታ) አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብኣዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብኣዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን ግጭት ማቆሙን በአዎንታ እንደምትቀበል እና አጥብቃም እንደምትደግፍ አስታወቀች።

መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብኣዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ትናንት ማሳወቁ ይታወሳል።

መግለጫ ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትናንት ባወጡት መግለጫ ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ የመንግሥት ውሳኔን ተከትሎ የተሳለጠ የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት እንደሚኖር ዕምነታቸውን ገልፀዋል።

የመንግሥት ውሳኔ ለትግራይ ክልል ብሎም ለሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወሳኝ እርምጃ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ለመላው ኢትዮጵያዊያን ደኅንነትና ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችል የፖለቲካ መፍትሄ ለመስጠትም መሰረት የሚሆን ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።

ሁሉም ወገኖች ይህንን ውሳኔ ዘላቂ የተኩስ አቁም ለማምጣት የሚያስችል ድርድርን ለማድረግ እንዲጠቀሙበት ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ ታቀርባለች ሲሉም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጣይ ሰላማዊ ጊዜን እንዲያሳልፍ አሜሪካ የቻለችውን ድጋፍ ሁሉ ማድረጓን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!