አሜሪካ ጄፍሪ ፊልትማንን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኝነታቸው አነሳች

ጄፍሪ ፊልትማን

ታኅሣሥ 29/2014 (ዋልታ) አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ጄፍሪ ፊልትማንን ከኃላፊነታቸው ማንሳቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን አስታወቁ።

አንቶኒ ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንደገለጹት ጄፍሪ ፊልትማን ተነስተው በምትካቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ተሹመዋል።

ፊልትማን ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሎ ቆይተዋል።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ዲፕሎማት ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ቀደም ሲልም በሳውዲ ዓረቢያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዚየ እና ሶሪያ በዲፕሎማትነት ያገለገሉ ሲሆን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትም የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።