አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተቀናጀ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ

ጥቅምት 20/2017(አዲስ ዋልታ) አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጨረቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና አመራሮች ጋር የወጭ ምርቶች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አካሄደዋል፡፡
በውይይቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጪ ያሉ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያላቸውን የውጭ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመጋበዝ ሀገራችን ያላትን ምቹ የገበያ ሁኔታ እንዲገነዘቡ የማድረግ ስራ መስራት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
የውጪ ገዥዎችን ለመሳብ በሚያደርጉት ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር በሚገጥማቸው ወቅት መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።