ነሐሴ 12/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ዘርፍ ማኅበር የቦርድ አባላት ጋር በአገራዊና የቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ስለሺ በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ስላለው የማሻሻያ ሥራ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአጎዋ የገበያ እድል እንደገና ተጠቃሚ እንድትሆን እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችንም አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ የንግድ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችን ከአሜሪካ ድርጅቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በጋራ ለመሥራት መግባባት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW