አምባሳደር ስለሺ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል በትኩረት እንሰራለን አሉ

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሻሻል በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ከዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ዲፕሎማቶች እና ሠራተኞች ጋር ትውውቅ ባደረጉበት ወቅት ነው።
አምባሳደር ስለሺ እንደገለጹት የሚሲዮኑ ባልደረቦች ዋና ትኩረት ዘመናትን ያስቆጠረው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል ሁሉን ዐቀፍ ጥረት ማድረግ ላይ ይሆናል።
በዳያስፖራ ተሳትፎ፣ ሕዝብ ለሕዝብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ገጽታ ግንባታ፣ ቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጎልበት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ከኢምባሲው እንደተገኘው መረጃ የሚሲዮኑ ባልደረቦች የአገራቱ ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረውን ዲፕሎማሲያዊ መስተጋብር የሚመጥን እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሙሉ አቅም እንሰራለን ብለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!