አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ከጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሾማቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ከዚህ ቀደም ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

ካገለገሉባቸው ኃላፊነቶች አምባሳደር ሽፈራው በቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኦዲትና አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊነት፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት እና በርዕሰ መስተዳደርነት መርተዋል፡፡

በተጨማሪም የትምህርት ሚኒስትር፣ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ሚኒስትር እና በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡