አምባሳደር ባጫ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫን ለፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አደረሱ

    አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ አዲስ ለተመረጡት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያስተላለፉትን የደስታ መግለጫ አደረሱ።

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በጋራ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አምባሳደር ባጫ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል።

በተለይም በልማት፣ ቀጣናዊ ሠላም እና ፀጥታ በማስፈን እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ትሥሥር ሀገራቱ ተቀራርበው መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!