አምባሳደር ታዬ በኒጀር የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንትነት ወር አፍሪካዊያን በክብር እንደሚስተናገዱ አምናለሁ አሉ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) ኒጀር የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የታኅሣሥ ፕሬዝዳንትነትን በመረከቧ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ኒጀር የታኅሣሥ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነት ሥራዋን ተረክባለች፡፡

አምባሳደር ታዬ በኒጀር ፕሬዝደንትነት እያንዳንዱ የአፍሪካ አገር በአክብሮት እንደሚስተናገድ እርግጠኞች ነን ብለዋል፡፡

ቋሚ መልዕክተኛው ለኒጀር መልካም ስኬት እንመኛለን ሲሉም በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡