አምባሳደር ታዬ ከመንግሥታቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከመንግሥታቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ሰርዋ ቴቴ ጋር ተወያዩ፡፡
አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ የሰብኣዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በተወሰደው የተኩስ ማቆም ውሳኔ እንዲሁም በቀጣናው ባሉ ድንበር ዘለል የፀጥታ ፈተናዎች እና መሰል ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!