አምባሳደር ነቢልና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የደኅንነት አማካሪ ተወያዩ

የካቲት 3/2014 (ዋልታ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የደኅንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ነቢል በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለአማካሪው ገለጻ አድርገዋል፡፡

ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉንም ያሳተፈ አገራዊ ውይይት ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅት እደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

አገራዊ ውይይቱ በኢትዮጵያ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መንግሥት ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡

መንግሥት ለዘላቂ ሰላም ጥረት ቢያደርግም ሕወሓት በአጎራባች ክልሎች እያደረሰ ያለውን ጥፋት መቀጠሉን አምባሳደሩ አብራርተዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የደኅንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት ድንበሮች ላይ ያለው የፀጥታ ሥራ እንዲጠናከር መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።