አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 11/2015 (ዋልታ) በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ጋር ውይይት አደረጉ።

አምባሳደር ዘነበ ከኮሚሽነር ተርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ አካላት ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡