አምባሳደር ዳባ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አቀረቡ

ሚያዚያ 21/2014 (ዋልታ) በሩዋንዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሩ ሚያዚያ 18/2014 ዓ.ም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ያቀረቡ ሲሆን በሁለቱ አገራት ታሪካዊ ግንኙነትና ወዳጅነት እንዲሁም በወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ አገራት ቀጣይ የድፕሎማሲ እና የወንድማዊ ግንኙነት ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡

በተመሳሳይም ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም የሹመት ደብዳቤ ቅጃቸውን ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታ ባቀረቡበት ወቅት በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ዳባ ፕሬዝዳንት ካጋሜ እና ባለቤታቸው በሩዋንዳ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ባዘጋጁው የእራት ግብዣ ላይም ታድመዋል።