አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ጎበኙ

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አስጎበኘ።

ለተለያዩ ሀገራት የተሾሙ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተው በሚሄዱባቸው የዓለም ሀገራት በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እንጂችሉ የተደረገ ጉብኝት ነው ተብሏል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዓለም ለማስተዋወቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የሥራ እንቅስቃሴዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና የወደፊት ሥራዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቧል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚረዳቸው አምባሳደሮቹ መግለጻቸውን ከኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡