አምኒስቲ ኢንትርናሽናል የራሴን ፎቶግራፍ ለተሳሳተ መረጃ ተጠቅሞበታል – ፎቶግራፈር አማኑዔል ስለሺ

ፎቶግራፈር አማኑዔል ስለሺ

ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – አምኒስቲ ኢንትርናሽናል በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ መንግስትን ለመወንጀል የተጠቀመበት ፎቶ የሀሰት መሆኑ ተጋለጠ።

የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ የሆነው አማኑኤል ስለሺ በቲውተር ገፁ እንዳስታወቀው፣ ፎቶው በኢትዮጵያ በተካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመሩ መራጮች በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ ሲደረግላቸው የሚያሳይ ነው ብሏል።

ይህን ፎቶ ግራፍ እኔ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያነሳሁት ነው ያለው ጋዜጠኛው፣ አምኒስቲ ኢንትርናሽል በተሳሳተ መንገድ መጠቀሙ እንዳሳዘነው ጠቅሷል።

ድርጊቱ ከሙያ ስነ-ምግባር ያፈነገጠና ስህተት ነው ሲል የገለፀው አማኑኤል፣ ተቋሙ ፎቶ ግራፉን እንዲያነሳው ጠይቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ኢትዮጵያን በሀሰት መረጃዎች ለመወንጀል እየተንቀሳቀሱ ነው።

አምንስቲ በትግራይ ክልል በንጹሀን ዜጎች ላይ እና በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ግድያ እና አፈናን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር አለመኖሩ የድርጅቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የጣለ ሌላ አጋጣሚ መሆኑንም የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል።