የአርሲ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 976 ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
ከተመራቂዎች ውስጥ 49 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ የሚመረቁ መሆናቸውን በዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ኩሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ገመዳ ሁንዴ ለዋልታ ገልጸዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተከታትለው የጨረሱ እንዲሁም ለ45 ቀናት የገጽ ለገጽ ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በክረምትና ኤክስቴንሽን የትምህርት መርኃግብር በ6 ኮሌጆችና አንድ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውንም ዶ/ር ገመዳ ጠቁመዋል፡፡
(በአድማሱ አራጋው)