አርቲስቶች የአረንጓዴ አሻራቸውን በአዳማ አሳረፉ

ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) – በአዳማ ከተማ በአባ ገዳ ፓርክ 100 የሚሆኑ አርቲስቶች የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሃይሌ ጀልዴ አርቲስቶች ችግኝ መትከላቸው ለሌላው ህዝብ ምሳሌ እንደሚሆን ጠቁመው በአዳማ ከተማ ብቻ አራት ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

(በሶሬቻ ቀበኔቻ)