አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ልማት፣ በቢግ ዳታ ፣ በሮቦቲክስና አቅም ግንባታ ዙሪያ አብሮ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ስምምነቱ የኮሚሽኑን አገልግሎቶች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለማዘመን ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ÷ከማዕከሉ ጋር አብሮ በመስራት ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የመሰሉ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ማፋጠን እንደሚገባ መናገራቸውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ያገኘነው መረጃ፡፡