አስቸኳይ የሰብኣዊ ድጋፍ ትግራይ እና አፋር ክልሎች መድረሱን አሜሪካ በአዎንታ ትመለከተዋለች – አንቶኒ ብሊንከን

አንቶኒ ብሊንከን

መጋቢት 24/2014 (ዋልታ) አስቸኳይ የሰብኣዊ ድጋፍ ትግራይ እና አፋር ክልሎች መድረሱን በአዎንታ እንደሚመለከቱት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ፡፡

ይህን መልካም ጅምር ማስቀጠል እንደሚገባና አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር ሁሉም ወገኖች የተጀመረውን አዎንታዊ እርምጃ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አማላክቷል።

ከሰሞኑ የዓለም ምግብ ድርጅት 500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዙ የሚታወስ ነው፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW