አሸባሪውን ሕወሓት ተጠያቂ ለማድረግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያሳድር እንደሚገባ ተገለፀ

ሌንጮ ለታ

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) የሰሞኑን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአሸባሪው ሕወሓት ጦር በአማራ ክልል ንፋስ መውጫ አካባቢ በፈፀማቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆን ጫና ሊያደርግ እንደሚገባ አንጋፋው ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ ገለጹ፡፡

አንጋፋው የኦሮሞ ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በአሸባሪው ሕወሓት ቀስቃሽነት የተጀመረው ጦርነትን ተከትሎ የተፈፀሙ ግድያ፣ ዘረፋና በቡድን ሴቶችን የመድፈር ወንጀሎችን በማጣራት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ለኢፕድ እንደገለጹት አሸባሪው ቡድን በፈፀማቸው ወንጀሎች ተጠያቂ እንዲሆን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጫና ማድረግ ይገባዋል፡፡ ጫና ብቻ ሳይሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግም አለበት ብለዋል፡፡

በጦርነት ወቅት በቡድን ሴቶችን መድፈር በዓለም አቀፍም ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው፡፡ በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ ዘንድም አስነዋሪ ድርጊት ነው።