አሸባሪውን ትሕነግ በግንባር ለመታገል መወሰናቸውን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) አሸባሪውን ትሕነግ በግንባር ለመታገል መወሰናቸውን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ግንባር የመዝመት ውሳኔን ተከትሎ ነው የጋራ ምክር ቤት አመራሮች ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል እወርዳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው ትሕነግ ግብዓተ መሬት ለማፋጠንና በግንባር ለመታገል መወሰናቸውንም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። አመራሮቹ በዛሬው ዕለት ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ውሳኔ ማርሽ ቀያሪ ነው ያሉት የጋራ ምክር ቤቱ አመራሮች በትግል ላይ ሳሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የፀጥታ አካላት የበግና የምግብ ድጋፍ አድርገዋል።

በተስፋዬ አባተ