ነሃሴ1/2013(ዋልታ) – አሸባሪው ህወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው ዕለት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሰላምና ብልፅግና ተልዕኮ ሊግ አስታወቀ።
ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተወጣጡ ወጣቶች የሚሳተፋበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ከ60ሺህ በላይ ወጣቶች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚገመት ተነግሯል።
ሰላማዊ ሰልፋ በዋናነት ህወሓት በሀገሪቱ ላይ የከፈተውን ግፍ የበዛበት ጦርነት የሚያወግዝ፤ ወጣቱ ሀገሩን ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአንድነት መነሳት እንደሚገባው የሚጠቁምና ህወሓት በሀገሪቱ ላይ እያሳደረ ያለውን በደል ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እንዲረዱት ያለመ መሆኑም ተነስቷል።
ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ መሰየሙ ይታወሳል።
(በዙፋን አምባቸው)