ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – አሸባሪው ህወሓት ከያሎና ጎሊና ወረዳዎች ተፈናቅለው ጋሊኮማ ጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት ተጠልለው በነበሩ አርብቶ አደሮች ላይ ጭፍጨፋ አካሂዷል።
የሽብር ቡድኑ በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ ዞን በኩል ባደረገው ትንኮሳ ከያሎ እና ጎሊና ወረዳዎች ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በጎሊና ወረዳ ጋሊኮማ የምትባል ቀበሌ በጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደር ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጭፍጨፋ ፈጽሟል።
ተፈናቃዮቹ በጊዚያዊነት ተጠልለውበት የነበረውን ጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት በማቃጠል በንፁሀን ህዝብ ላይ አረመኔያዊ ጥቃት በመፈፀም አስከፊ ስራውን አከናውኗል፡፡
ጁንታው በተጨማሪም ለተፈናቃዮች በጋሊኮማ የሚገኘውን የምግብ መጋዘን በከባድ መሳሪያ አጋይቶታል፡፡
በትንኮሳው መጋዘኑ ውስጥ የነበረ ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች የቀረበ አስቸኳይ የምግብና አልባሳት እርዳታ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡