አሸባሪው ህወሓት በአንድ ቤት ውስጥ የነበሩ 10 ንጹሀን ዜጎችን በግፍ መግደሉ ተገለጸ

ነሐሴ 30/2014 (ዋልታ) የአሸባሪ ህወሓት ቡድን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰቆጣ ወረዳ ልዩ ስሙ ወለህ በሚባል አካባቢ 10 ንጹሃን ዜጎችን በግፍ መጨፍጨፉን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

ወ/ሮ ለምለም አዳነ የወለህ ማርያም ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ልጆቻቸውን ለማሳደግ፣ ለማስተማርና ለቁም ነገር ለማድረስ ደፋ ቀና እያሉ በነበሩበት ስዓት በጭካኔ የተሞላው እና ለንጹሃን የማይራራው የሽብር ቡደኑ ከነ ልጆቻቸው በጭካኔ ገድሏቸዋል ነው የተባለው።

ከተገደሉት ንጹሃን ዜጎች መካከል ሰባቱ ወ/ሮ ለምለም አዳነ እና 6 ልጆቻቸው ሲሆኑ ሌሎቹ 3ቱ ደግሞ ተፈናቃዮች መሆናቸው ታውቋል።

የሰላም ድርድሩን ወደ ጎን በማለት ድጋሚ ነፍጥ ያነሳው የሽብር ቡድኑ ህወሓት ሰላማዊ የሆኑና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሴት እና ሕፃናትን በከባድ መሳሪያ ጨፍጭፎ መግደሉን አሚኮ ዘግቧል።

ይህ የአሸባሪ ቡድኑ የጭካኔ ድርጊት፣ ከሰላም ይልቅ ለጦርነት እጁን የዘረጋ፣ የሀገሪቱ ዜጎች በሰላም እንዳይኖሩ የወጠነ ጨፍጫፊ ቡድን መሆኑን ያሳያል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW