አሸባሪው ሕወሓት በመኪና የሚደርሰውን ሰብኣዊ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ማገዱ ተገለፀ

ጥር 19/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በመኪና የሚደርሰውን የሰብኣዊ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ማገዱን በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለፁ፡፡

አምባሳደር ታዬ በቲውተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ቡድኑ በአፋር ክልል በአባላና ማጋሌ፣ ባራህሌ እና ኢሬብቲ አካባቢዎች በፈጸመው ጥቃት ከ200 ሺሕ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡

ቡድኑ የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት ለአካባቢው ነዋሪዎች ለማድረስ የሚደረገውን ጥረትም አስቸጋሪ እንዳደረገው አስታውቀዋል፡፡

አዲስ ጥቃት በመክፈቱም በመኪና ይደርስ የነበረውን የሰብኣዊ እርዳታን ሙሉ በሙሉ ማገዱን  ለመንግሥታቱ የፀጥታው ምክር ቤት አስረድተዋል።