ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ህወሓት ሰዎችን በፍርሃት እንዲሸበሩ በማድረግ እና በጥቅማ ጥቅም በመደለል የፖለቲካ ስልጣኑን ለመያዝ ሙከራ እያደረገ ይገኛል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ውስጥ አሁንም በሴፍቲኔት ፕሮግራም ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቢሆኑም፣ ላለፉት 27 ዓመታት የአገሪቱን ሲመራ የቆየው አሸባሪው ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ ደህንነት ፍፁም ደንታ እንደሌለው ማሳያ ነው ብሏል።
አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ጎንደር እና በወሎ አካባቢዎች የመንግሥትን የገለልተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማከማቻዎችን በማፍረስ በወረሩባቸው አካባቢዎች፣ ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጠላትነት በድጋሚ አረጋግጧል።
ሕወሓት የብዙ አባወራዎችን ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ለማበላሸት ያለመ እንደሆነ ከተያዙት የሰሜን ወሎ እና የጎንደር አጎራባች አካባቢዎች የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
በቅርቡ በተያዙ ግዛቶች፣ አሸባሪው ህወሓት እና ተከታዮቻቸው የደረሱ ሰብሎችን እየሰረቁ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፣ አሸባሪ ቡድኑ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የአርሶ አደሮችን ንብረት ዘርፏል፤ የምግብ እርዳታ መጋዘኖችንም አውድሟል ነው የተባለው፡፡
ቡድኑ ትምህርት ቤቶችን እና ኮሌጆችን፣ ባንኮችን፣ ጤና ጣቢያዎችን፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች ተቋማት ሆን ብሎ አውድሟል፡፡ ለአብነትም የአዋሽ ወልዲያ/ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት መውደሙ የሚታወቅ ነው፡፡
መንግስት ፈጣን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲደረግም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ መቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።