አሸባሪው ሕወሓት በሸዋሮቢት ከተማ ታሪክ የማይዘነጋቸውን ግፎች ፈፅሟል

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) በሸዋሮቢት ከተማ የሚገኙ መድኃኒት ቤቶች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች፣ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር ተዘርፈዋል፤ ከዘረፋ የተረፉት ደግሞ ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርገው ወድመዋል።
የከተማዋ ነዋሪ የውብዳር መሀመድ የሽብር ቡድኑ ከተላላኪው ሸኔ ጋር በመተባበር ከተማዋን አውድሟታል ብለዋል።
“ሃብትና ንብረት ይተካል” የሚሉት የውብዳር ወራሪው ንጹሃንን በአደባባይ በመረሸን የጭካኔውን ጥግ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ወራሪዎች መነኩሴ ሳይቀር በመድፈር ነውረኝነታቸውን አሳይተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“የአሸባሪው ሕወሓት ወራሪዎች አንዲትን ሴት ስምንት ሆነው በመድፈር ለሰው ልጅ አዕምሮ የሚከብድ ኢሰብኣዊ ድርጊት መፈጸማቸውንም ተናግረዋል።