አሸባሪው ሕወሓት በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ407 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ407 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የደረሰውን ውድመት ጎብኝተዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አሸባሪው ቡድን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ያደረሰው ጥፋት የቡድኑን ፀረ ሕዝብነት የሚገልጽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም የወደሙ ንብረቶችን መልሶ በመተካት በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ይደረጋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡