አሸባሪው ሕወሓት የምርኮኞች ምስል በማለት ያሰራጨው ቪዲዮ ሀሰተኛ ነው

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት የምርኮኞች ምስል በማለት በመገናኛ ብዙኃን ያሰራጨው ቪዲዮ ዓላማው በሃሰተኛ በተቀነባበረ ምስል ዜጎችን የማደናገር ሙከራ ነው ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ገለጸ፡፡
አሸባሪው ሕወሓት የራሱን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ልብስ አልብሶ፣ በተጨማሪም በወረራ ከአማራና ከአፋር ክልል የወሰዳቸውን ወጣቶችና ከጦር ተመላሾች በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ አምርቶ ተንቤን የደበቃቸውን የደንብ ልብሶች ካለበሰ በኋላ ጥቂቱን የሰው ብዛት በፊልም ኤዲቲንግ በማባዛት ለዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን ግብዓትነት በመስጠት ላይ ይገኛል ብሏል፡፡