የካቲት 14/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ክልል በሚገኙ የውሃ ተቋማት ላይ እስከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ውድመት ማድረሱን የክልሉ ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ቢሮው ከሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ከወረዳ ጽሕፈት ቤት ባለድርሻዎች ጋር በኮምቦልቻ ከተማ እየተወያየ ነው፡፡
በውይይቱ በከተሞች ብቻ 102 የውሃ ተቋማት ውድመት የደረሰባቸው ቢሆንም በመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ርብርብ አብዛኞቹ ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል ነው የተባለው።
ጉዳት የደረሰባቸው የገጠር የውሃ ተቋማት ወደ ነባር አገልግሎታቸው ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ መገለጹን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
ለዚህም ክልሉ በርካታ ፓምፖች እና ተጨማሪ ግብአቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነስቷል፡፡
በውይይቱ የክልሉ ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ለወረዳ ውሃ ጽሕፈት ቤቶች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉም ተመላክቷል፡፡