አሸባሪው ትሕነግ የሚያሰራጨውን የውሸት ፕሮፖጋንዳ በማጋለጥ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

ሄኖክ ስዩም (ዶ/ር)

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – አሸባሪው ትሕነግ የሚያሰራጨውን የውሸት ፕሮፖጋንዳ በማጋለጥ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

ከሽብር ቡድኑ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሰሩ የሚገኙ ምዕራባዊያን አገራት መገናኛ ብዙኃንን የድብቅ አጀንዳቸው ማስፈፀሚያ እያደረጉ መሆኑን ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን ገልፀዋል፡፡

ይህንን ሀቅ መጋፈጥ ያስፈልጋል የሚሉት የፓሊሲና የሕዝብ አስተዳደር ተመራማሪው ሄኖክ ስዩም (ዶ/ር) አሸባሪው ትሕነግ የሚያሰራጫቸውን መረጃዎች ስህተትነት በመረጃ አስደግፎ መሞገትና እውነትን መግለጥ እንደሚገባ ያነሳሉ፡፡

ተመስገን ቶማስ (ዶ/ር)

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላምና ደኅንነት መምህርና ተመራማሪው ተመስገን ቶማስ (ዶ/ር) የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የዓለም ዐቀፉን ማኅበረሰብ ስለማሳታቸው አስታውሰዋል፡፡ ይህን ለመቀልበስም ኢትዮጵያዊያን የማኅበራዊ ትስስር ገፆችን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ላይ ሊበረቱ ይገባል ብለዋል፡፡

(በሱራፌል መንግሥቴ)