አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሁመራ በኩል 12 ጊዜ የማጥቃት ሙከራ ቢያደርግም ተደምስሷል

ነሀሴ 14/2013 (ዋልታ) – አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሁመራ በኩል 12 ጊዜ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርግም በሕዝቡና በፀጥታ አካላት ትብብር መደምሰሱን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ገለጹ።

ኮሎኔል ደመቀ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሁመራ በኩል ለ12 ጊዜ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ቢያደርግም በሕዝቡና በፀጥታ ሀይል ትብብር መደምሱንን ተናግረዋል።

ቡድኑ ዳግም በሁመራ በኩል ጥቃት ለማድረስ ቢሞክር መቀበሪያው ይሆናል ነው ያሉት ኮሎኔሉ።

የአካባቢው ማኅበረሰብ በቂ ዝግጅት በማድረግ አሸባሪውን ቡድን የመደምሰስ አቅም ላይ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።