• የከሚሴ አካባቢ በመከላከያ ከበባ ውስጥ ገብቷል
• መንግሥት አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተቃውሟል
ኅዳር 4/2014 (ዋልታ) ወራሪው የሕወሓት ቡድን በወረራ የያዛቸውን የተለያዩ አካባቢዎች በወገን ጦር ተጋድሎ ማስመለስ እየተቻለ መሆኑን መንግሥት ገለፀ፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መግለጫ እየሰጡ ነውው፡፡
ዜጎች መሬታቸውን፣ ነፃነታቸውንና አገራቸውን ለማስከበር እያደረጉ ያለው እንቅስቅሴ ሊወደስ የሚገባው በመሆኑ ይህንኑ እንቅስቃሴም ወራሪው እና አሸባሪው ሕወሓት ከኢትዮጵያ ምድር እስኪወገድ ድረስ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል፡፡
በአፋር ክልል ወራሪው የሕወሓት ቡድን ከፍተኛ ጥቃትን አድርሷል ሆኖም ጀግናው የአፋር ሚሊሻ የጠላት ሀይልን ድባቅ መትቷል ተብሏል፡፡
የወገን ጦርም በአሸባሪው ቡድን የሚቃጣበትን ጥቃት ከመመከት ባለፈ በወራሪው ተወስዶበት የነበረውን ይዞታ እያስመለሰ ይገኛል ተብሏል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊት በእግረኛና በአየር ኃይል ከሚሴን ከበባ ውስጥ አስገብቷል ነው የተባለው፡፡
በኦሮሚያ በአንዳንድ አካባቢዎች የአሸባሪው ሸኔ እንቅስቃሴ ነበር ሆኖም በምስራቅ ወለጋ ሰሜን ሸዋ ምዕራብ ወለጋ የሸኔን እንቅስቅሴ ለማጥራት በተወሰደ እርምጃ የቡድኑን አከርካሪ መምታት ተችሏል፡፡
ሸኔ መቀመጫው ባደረጋቸው አንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎችንም ከቡድኑ ነፃ ማውጣት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ ላይ እየበረታ የመጣውን ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን ይህን በመመከት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ፅንፍ የያዙት ምእራባውያን በመገናኛ ብዙኃናቸው የሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀውሶች እየተባባሱ መምጣታቸውን በመዘገብ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት አንድን አካል ለማጥፋት መሰረት ያደረገ ጥቃት እያደረሰ ነው በሚል እየኮነኑ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳወቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ዩቲዩበሮችን በማገድም በግልፅ ጥላቻቸውን እያሳዩ ይገኛል ተብሏል፡፡
እንዲሁም አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግሥት ታካ የኤርትራ መንግሥት ላይ ያሳለፈችውን ማእቀብ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያወግዝም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በሄብሮን ዋልታው