አሸባሪዎውን ኦነግ ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ በሰበታ ከተማ ተካሄደ

ነሃሴ12/13(ዋልታ) – አሸባሪዎውን ኦነግ ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ በሰበታ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ኦነግ ሸኔ ቀደም ሲል በህውሀት አገዛዝ ዘመን የደረሰበትን ግፍ እና መገፋት ወደ ጎን ትቶ ከቡድኑ ጋር ጥምረትን የመረጠው ሀገር የማፍረስ አላማ አንድ ስላደረጋቸው ነው ያሉት የሰበታ ከተማ ከንቲባ ብርሀኑ በቀለ ይሁንና ኢትዮጵያ በጀግኖች አባቶች አጥንት የታጠረች ሀገር በመሆኗ በጠላት ሴራ አትፈርስም ብለዋል::
የሽብር ቡድኑ ሀገርን ለማፍረስ የያዘውን ግብ ሁሉም ኢትዮዽያዊ ዜጋ በጋራ እና በተባበረ ክንድ ሊመክተው ይገባል ተብሏል::
የአያት ቅድመ አያቶቻችን የአልበገሬነት ወላፈን ጠላቶቻችንን ዶጋ አመድ ለማድረግ ቢበዛ እንጂ አያንስም ያሉት ከንቲባው ይህ ትውልድም ባንዳንና ሀገር ሻጮችን በመመከት የኢትዮጵያምን ቀጣይነት ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል::
የሀገር ደጀን የሆነው የመከላከያ ሰራዊት መተኪያ የሌለው ህይወቱን አቋርጦ ሀገር እንድትቀጥል እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለመደገፍ ሁሉም ዜጋ አበርክቶውን እንዲያክል ተጠይቋል::
አሸባሪዎቹ የህውሀት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ ጥምረት ኢትዮዽያን ለማፍረስ ያለመ ነው ይህን ህልማቸውን ቅዠት ለማድረግ ወደ ኋላ አንልም ሲሉ የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል::
(በሄብሮን ዋልታው)