ጥር 1/2015 (ዋልታ) በጦርነት ምክንያት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት በመድረሱ ኃይል ከሁለት ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረው የአብኣላ ከተማና አካባቢው ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡
አገልግሎቱን እንደገና ለመመለስ በተደረገ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ጥገና ከተማዋ ዳግም ኤሌክትሪክ ማግኘት እንድትችል ተደርጓል፡፡
ከተማው ከመቀሌ ሰብስቴሽን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ሲያገኝ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ በደረሰ ከፍተኛ ጉዳት ተቋርጦ መቆየቱንና በዚህም የመካከለኛና የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ትራንስፈርመሮች እንደገና በመጠገን አገልግሎቱ ዳግም መመለስ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡
ቀሪ በኪልበቲ ረሱ የሚያገኙ ከተሞች ለማገናኘት እየተሰራ ይገኛልም ተብሏል፡፡