አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ክብረ ወሰኑን በማሻሻል ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ

አትሌት ታምራት ቶላ

ሐምሌ 11/2014 (ዋልታ) አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ክብረ ወሰን በማሻሻል ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች ማራቶን ዛሬ ሲደረግ ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ የዓለም ሻምፒዮናውን የማራቶን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር ነው አሸናፊ የሆነው፡፡

አትሌት ታምራት ማራቶኑን ሮጦ ለማጠናቀቅ 2፡05፡36 የሆነ ሰዓት ፈጅቶበታል፡፡

አትሌት ሞስነት ገረመው ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድርሩን ያጠናቀቀ ሲሆን በዚህም ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ሞስግነት ገረመው ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2፡06፡42 የሆነ ሰዓትም ፈጅቶበታል፡፡

በውድድሩ ተሳፎ የነበረ ሰይፉ ቱራ 6ኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ !!

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW