አትሌት ኃይሌ ችግሮቻችንን እንዴት መፍታት እንደምንችል የምናውቅ ሕዝብ ነን አለ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን እንዴት ችግሮቻችንን መፍታት እንዳለብን ጠንቅቀን የምናውቅ ሕዝብ ነን ሲል አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ገለፀ፡፡

“የኢትዮጵያን ሕዝብ አታውቁትም፤ እኛ ኢዮጵያዊያንን አታውቁንም እኛ የምነለይ ሕዝብ ነን“ ሲል አትሌት ኃይሌ ባስተላለፈው መልእክት ተናግሯል፡፡

አትሌት ኃይሌ በአገሪቱ አለመረጋጋት እና ጦርነት ቢኖርም እንኳን እንዴት ማረጋጋት እና ችግሮቻችን መፍታት እንዳለብን ጠንቅቀን የምናውቅ ሕዝብን ነን ሲል ነው ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በእንግሊዘኛ ባስተላለፈው መልዕክት ያሳወቀው፡፡

ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት ያለት መሆኑን ያስታወሰው አትሌት ኃይሌ የአሜሪካ መንግሥት እና አንዳንድ የምዕራባዊያን አገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያለችሁን ግንኙነት የምታሳዩት እንዲህ ነው ወይ? ሲልም ጠይቋል፡፡

አትሌት ኃይሌ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ታሪክ ሆኖ እንደሚቀር በመጥቀስ አገራቱ ለረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነታቸውን ከግምት እንዲያስገቡም አሳስቧል፡፡
በትዝታ መንግሥቱ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!