አትሌት ደራርቱ ቱሉ ባህር ዳር ገቡ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬታቸውን ለመቀበል ባህር ዳር ገቡ።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር ለሚኖሩት እንዲሁም ሰውን በሰውነቱ ብቻ ላከበሩት ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በስፖርቱ ዓለም ከማስጠራት ጀምራ ለኅብረሰተብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት ለምትተጋው ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት በነገው እለት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሃኒ አበበ (ከባህር ዳር)