አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ጋር በስልክ ውይይት  አድርገዋል።

ሚኒሰቴሩ ባደረጉት የስልክ ውይይት ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በሰሜን የአገራችን ክፍል በተሳካ ሁኔታ የተካሄው የህግ የበላይነት ማስከበር ዘመቻ፣ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተካሄደ ያለውን ተግባር፣ የህወሃት ጁንታ ያፈረሳቸወን መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመጠገን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተካሄደ ያለው ጥረትና በጥረቱ የተገኙ ውጤቶች፣ የኤርትራ ስደተኞችን አያያዝ፣ በማይካድራና ሌሎች አካባቢዎች  የተፈፀሙ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችና  ድርጊቶቹን ለማጣራት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች፣ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለህግ  ለማቅረብ እየተደረገ ያለውን  እንቅስቃሴ እንዲሁም፤ በአጠቃላይ  በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲፈጠር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በዝርዝር  አስረድተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር  በትብብር ለመሥራት ያላትንም ጽኑ ፍላጎት ገልፀዋል።

ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ በበኩላቸው፣  የኢትዮጵያ ስኬት የአሜሪካ ስኬት መሆኑን ገልፀው፣ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር ያለውን በጎ ስሜት ገልፀዋል።

ኢትዮጰያ ያጋጠማትን ችግር ለመቋቋም እያደረገች ያለውን ጥረትና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላደረጉላቸው ገለፃ አመስግነዋል።

መረጃውን ያገኘነው ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው፡፡