አንዲት እናት ድምጽ ከሰጡ በኋላ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላገሉ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ አንዲት እናት ድምፅ ለመስጠት በሄዱበት የጀመራቸውን ምጥ ድምጽ ከሰጡ በኋላ በሰላም ተገላገሉ፡፡

አበራሽ ጉታ የተባሉት መራጭ ድምፅ ለመስጠት በሄዱበት ሄጦሳ ዙሪያ ምርጫ ጣቢያ ነው ምጥ የጀመራቸው፡፡

እንደምንም ድምፅ ከሰጡ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም በማቅናት ወንድ ልጅ መገላገላቸው ተገልጿል፡፡

ለልጃቸውም ታሪኩ የሚል ስያሜ ሰጥተዋል ሲል የሄጦሳ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል፡፡