አዋሽ ባንክ ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን በሚል የደንበኞችን ሳምንት እንደሚያከብር ገለጸ

የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሺፈራው

መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) አዋሽ ባንክ ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን በሚል መርህ የደንበኞችን ሳምንት እንደሚያከብር ገለጸ።

የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሺፈራው ባንኩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ በመሆን ከ680 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት ከገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህም ከ6.8 ሚሊየን በላይ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞችን ማፍራት እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ባንኩ 116 ቢሊየን ብር በላይ የተቀማጭ ሂሳብ ማሰባሰብ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

አዋሽ ባንክ ከዛሬ መጋቢት 6/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚያከብረው የደንበኞች ሳምንት ሶስት ዓላማዎች እንዳሉት የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ደንበኞችን ማመስገን፣ ማክበር እና ማወደስ እንዲሁም የደንበኞችን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ቀዳሚ ናቸው ብለዋል።

በሳምንቱ የባንኩ የዋና መስሪያ ቤት ኃላፊዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ባንኮች ተመድበው የደንበኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ያሉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ለላቀ የደንበኛ አገልግሎት ይተጋሉም ተብሏል።

በቁምነገር አሕመድ

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!