አዋሽ ባንክ በይቆጥቡ፤ ይሸለሙ መርኃ-ግብር ባለእድለኞችን ሸለመ

መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) አዋሽ ባንክ 9ኛ ዙር “በአዋሽ ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይሸለሙ” መርኃ-ግብር ለባለእድለኞች ሽልማት አበርክቷል።

ባንኩ መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ባወጣው እጣ መሰረት ለእድለኞች የሽልማት ርክክብ አድርጓል።

የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሽፈራው መርኃ-ግብሩ የማኅበረሰቡን የቁጠባ ባህል ከፍ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

በመርኃ-ግብሩ 5 የሽልማት አይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን 1 የጭነት አይሱዙ፣ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል፣ ላፕቶፕ፣ 32 ኢንች ኤልዲ ቴሌቪዥንና የተለያዩ ስልኮች ለእድለኞች ተሸልመዋል።