አዋሽ ባንክ ከ5.5 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ

ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – አዋሽ ባንክ በ2012/13 ዓ.ም 5.58 ቢሊየን ብር አመታዊ ትርፍ ማግኘቱን አሰታወቀ።

የአዋሽ ባንክ ዋና ሰራ አስፈፃሚ ፀሃይ ሽፈራዉ የባንኩን አመታዊ ትርፍ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በአመቱ የኮሮና ቨይረስን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የነበሩ ያለመረጋጋት ችግሮች ተግዳሮት ቢሆኑም መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረትና ድጋፍ ባንኩ ትርፋማ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

ባንኩ በተያዘዉ አመት 100 የሚደርሱ አዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን ከሁለት ሚሊየን በላይ አዲስ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞችን በማፍራት ጠቅላላ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞችን ከአምስት ሚሊየን በላይ ማድረሱን ገልጿል።

የባንኩም አጠቃላይ ተቀማጭ ሂሳብ 107 ነጥብ 7 ቢሊየን መድረሱን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ አስታውቀዋል።

(በህይወት አክሊሉ)