አዲስ ለተሸሙ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) በአዲሱ መንግስት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራሩ በንፁህ እጅና በቅንነት ሀገሩን ማገልገል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በአግባቡ በማልማትና በትጋት በመስራት ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አመራሮች ከስልጠናው በኋላም የዓላማ ጽናት በቡድን የመስራት መንፈስና በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡