አዲስ አበባን በመወከል በዓለም አቀፍ  የስእል ውድድር ያሸነፉ ታዳጊዎች

መስከረም 7/2014 (ዋልታ) አዲስ አበባን በመወከል በደቡብ ኮሪያዋ ቹንቹን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የስእል ውድድር አሸናፊ የሆኑ ታዳጊዎች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ የሆኑት ኪም ሂዮን ዱ በቹንቹን ከተማ ከንቲባ ስም ሽልማቱን ለአሸናፊ ታዳጊዎቹ አስረክበዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊ ወዳጅነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ ኪም ሂዮን ዱ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና ቹንቹን ከተሞች መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።