አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና የግብርና ኮሌጅ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

መስከረም 30/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንስሳት ህክምናና የግብርና ኮሌጅ በእንስሳት ህክምና ያሰለጠናቸውን 152 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
ዩኒቨርሲቲው 10 በሶስተኛ ድግሪ እንዲሁም 45 በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን ነው የሚያስመርቀው፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ኮሌጅ ዲን ፕሮፌሰር ሂካ ዋቅቶሌ የድህረ ተመራቂዎችን ቁጥር የማሳደግ አቅጣጫ በመቀበል ከሁለተኛ ድግሪ በላይ የሚሰጣቸውን የትምህርት ዘርፎች በማስፋፋት ላይ ነው ይገኛል ብለዋል።
ኮሌጁ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ከማስመረቅ በላፈ በምርምር ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በዘንድሮ ዓመት ብቻ 132 የምርምር ውጤቶችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትሟል ተብሏል።
በምርቃ ስነሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሀና (ፕሮፌሰር)ን ጨምሮ ሌሎች የዘርፉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በመስከረም ቸርነት