“አድዋ በደም የተገኘ ነፃነት ነው፤ አግዋ ግን እርዳታ ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥቅምት 28/2014 (ዋልታ) “አድዋ በደም የተገኘ ነፃነት ነው፤ አግዋ ግን እርዳታ ነው” ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባ አዳነች አሸባሪውን ሕወሓትና አጋሮቹን ለማውገዝ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው ሰልፍ ላይ በነፃነታችንና ሉኣላዊነታችን ላይ የሚመጣ መንኛውም ጉዳይ ተቀባይነት የለውም ብልዋል።

አገር ለማፍረስ ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር የቆሙ ኃይሎች በመገናኛ ብዙኃናቸው በሚነዙት ሽብርም አንበረግግም ያሉት ከንቲባዋ አዲስ አበባ የተከበበችው በድንቅ ጀግኖች ልጆቿ መሆኑን ይወቁት ብለዋል። የተመኙትም አይስካም ብለዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት አብረውት ከተሰለፉ የወገን ኃይሎች ጋር በመሆን ዛሬ ላይ ድል እየተቀዳጀ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የሽብር ቡድኑን ግብኣተ መሬት የበለጠ ለማፋጠንና ለአገራችን ነፃነት ዛሬ ነገ ሳንል መዝመት አለብንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ድል ቅርብ ነውና ውሎ ሳያድር በዚች ታሪካዊ (መስቀል አደባባይ) ቦታ በድጋሚ በድል እንገናኛለን ሲሉም ተናግረዋል።
በደምሰው በነበሩ