አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ

ሐምሌ 21/2015 (ዋልታ) ባለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናውን ያቀረበው የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ቅዳሜና እሁድ ወደ መፈተኛ ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እንደሚገቡ እና መጪው ሰኞ ደግሞ ገለጻ እንደሚሰጣቸው ጠቁሟል፡፡

ፈተናቸውን ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡