አፈ-ጉባኤዋ የምክር ቤቱ አባላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ መወጣት እንዳለባቸው አሳሰቡ

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የምክር ቤቱ አባላት ከሕዝብ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ መወጣት እንዳለባቸው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ አሳሰቡ፡፡

ምክር ቤቱ በ6ኛ ምርጫ ዘመን 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት የ9 ወራት ሪፖርት ቀርቦ በድክመት እና በጥንካሬው ላይ ውይይት እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

በክልሉ ርዕስ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት የ9 ወራት ሪፖርት እየቀረበ መሆኑን ከሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡