መስከረም 11/2014 (ዋልታ) – በቅርቡ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አከባበር አስመልክቶ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
ኢሬቻ የኦሮሞ ኅብረትና አንድነት ማሳያ ሲሆን በዓሉን ከብሔሩ ተወላጆች ውጭ ያሉም የሚሳተፉበት መሆኑን በውይይቱ አከባበሩን አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት ብርሀኑ ባይሳ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ኢሬቻ ከማኅበራዊና ከቱሪዝም አኳያ ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳው የጎላ እንደሆነም ተገልጿል።
የኢሬቻን በዓል ለእኩይ ዓላማቸው መፈፀሚያ ሊያደርጉ የሚፈልጉትን አካላት መከላከል እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል፡፡
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባና ቢሾፍቱ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ የተሳታፊዎች ቁጥር ሳይገደብ እንዲከበር የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት መወሰኑ ይታወሳል፡፡
(በሀኒ አበበ)