ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት በኢፌዴሪ መከላከያ የሜካናይዝድ ማስተባበሪያ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምእሸት ደግፌ እና የታንዛኒያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ሌ/ጀኔራል ማስዪ ሚክንጉሌ መሆናቸው ተገልጿል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በወታደራዊው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ሌ/ጀኔራል  አለምእሸት ደግፌ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ሌ/ጄ ማስዪ ሚክንጉሌ  በበኩላቸው የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት ለአገራቱም ሆነ ለቀታናው ሰላምና ደኅንነት መጎልበት የራሱ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አመልክተው ለልዑካን ቡድኑ ለተደረገው አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።